የኢኮኖሚ ፍሪደም ፋየርስ ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ በእንግሊዝ ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት በቪዛ ምክንያት ከጉዞ መታገዳቸውን መርህ አልባ ሲሉ ተችተውታል።
የምዕራባውያን ኢምፔሪያሊዝም ሃገር አሳጥቶናል በማለት አጥብቀው የሚተቹት እና በደቡብ አፍሪካ የነጮች የመሬት ይዞታ በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆን አለበት ብለው የሚሞግቱት ማሌማ ጉዳዩ እንዳስገረማቸው ተናግረዋል።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው እንግሊዝ ለውሳኔዋ ምንም ዓይነት “ትክክለኛ ማረጋገጫ” እንደሌላት ተናግረው “የተቃርኖ ፖለቲካ አመለካከትን ለማፈን ሙከራ አድርጋብኛለች ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በደቡብ አፍሪካ የእንግሊዝ ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት አንቶኒ ፊሊፕሰን ለጁሌስ ማሌማ ምክትል በፃፉት ደብዳቤ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተቃዋሚ መሪው ቪዛ ያልተሰጣቸው የቪዛ ማመልከቻው ቶሎ ባለመድረሱ ነው ሲሉ አስተባብለዋል።
ጁሌስ ማሌማ ግን የእንግሊዝ መንግስት ሆን ብሎ ቪዛ እንደከለከላቸው በመግለጽ፣ ከአንዱ ሀገር ወደሌላ ሀገር የመንቀሳቀስ መብቴን ነው የገፈፉት በማለት መተቸታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ምላሽ ይስጡ