👉ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50 ሺ (ሃምሳ ሺ ብር ) የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡
👉በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዪ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ሰው ብር 100 ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር ) እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
👉በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዪ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር ) የሚበልጥ ከሆነ የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
👉ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር ) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
👉ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር ) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ የሚጣለውን ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
👉ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300 ሺ (ሥስት መቶ ሺ ብር ) እስከ ብር 500ሺ ብር ) የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
👉ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ አትሞ ጥፋተኛ የተባለ ሰው ለሁለተኛ ጊዜ ወንጀሉን ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፍቃዱም ይሰረዛል፡፡
(የገቢዎች ሚኒስቴር)
ምላሽ ይስጡ