6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ27ኛ መደበኛ ስብሰባው በምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮችን ሰይሟል፡፡
አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የምክር ቤቱን የአባላትና ስነምግባር ደንብ መሰረት አድርገው በምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮችን ለመሰየም የሚያስችላቸውን የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
በዚሁ መሰረትም ፕሮፌሰር መሐመድ አብዱ የከተማ፣ መሰረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ መለስ መና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙ ሲሆን፤ የውሳኔ ሀሳቡም በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡


ምላሽ ይስጡ