የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን እና በዚህም ቤተክርስቲያኗ የተሰማትን ሀዘን ገልጻለች።
ቤተክርስቲያኗ በማህበራዊ ትስስር ገጿ ባወጣችው የሀዘን መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ዛሬ በሰማነው እጅግ አሳዛኝ ዜና የብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዚህ አለም ድካም ማረፍ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን ብላለች።
በዚህም መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ ለቅዱስ አባታችን ዘለዓለማዊ እረፍት በጸሎት አብራችሁ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን ስትልም ጥሪ ማቅረቧን ኢዜአ ዘግቧል።
ምላሽ ይስጡ