ለእርዳታ ከውጭ የሚገቡ የምግብና የህክምና መሳሪያዎችን የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ቢሆንም ሁሉም የእርዳታ መሳሪያዎችና የምግብ ድጋፎች በማህበረሰቡ ዘንድ ችግር የሌለባቸው መምሰሉ የግንዛቤ ክፍተትን እንደፈጠረ በኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የህክምና መሳሪያዎች ምዝገባና ፈቃድ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ታከለ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡
የእርዳታ ድርጅቶች በተለያዩ ጊዜያት በተለይ ወረርሽኝ ሲኖር፣ መንግስት የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲደገፉ ጥሪ ሲያደርግ የሰበአዊ ድጋፎች ወደ ሃገር እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡ አክለውም በሃገር አቀፍ ደረጃ ያልተመዘገቡ የእርዳታ ምርቶች ወይም የምግብ ድጋፎች በአስቸኳይ አደጋ ጊዜ ድጋፍ በሚል እንደሚገቡ ገልጸው፣ በጤና ሚንስቴር በኩልም የህክምና መሳሪያዎች ና መድሃኒቶች በተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች አማካኝነት እንደሚለገሱም ጠቅሰዋል፡፡
እነዚህ እና መሰል አይነት ድጋፎች ወደ ሃገር ሲገቡ በተለያዩ መመዘኛዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ ክትትል አድርጎባቸዉ እንዳይገቡ በሚታገዱበት ወቅት በማህበረሰቡ በኩል ከፍተኛ የግንዛቤ ክፍተቶች እንዳሉ እና በእርዳታ የተገኘ ነገር ሁሉ ጥሩ እንደሆነ አድርጎ የማሰብ ነገር በማህበረሰቡ መለመዱ ከፍተኛ ችግር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
በእርዳታም ሆነ በሃገር ውስጥ አስመጭ ነጋዴዎች የሚገቡ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችንም ይሁን ምግብ ነክ የሆኑ ነገሮች የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈ ከሆነ አደጋው የከፋ ስለሚሆን ማህበረሰቡና የሚድያ አካላት በሙሉ እገዛ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ