በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በ2017 ዓ.ም በሶስት ዙር የተማሪዎች ምዝገባ የተካሄደ ሲሆን በተካሄደው ምዝገባም ከሰባት ሚሊዬን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 2.8 ሚሊየን ተማሪዎችን ብቻ መመዝገብ መቻሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ተመዝግበውም በተገቢዉ መልኩ ትምህርታቸውን የማይከታተሉ በርካታ መሆናቸው የገለጹት የክልሉ ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ናቸው። በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ የመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን በማንሳት የተመዘገቡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በክልሉ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ለማድረግ ንቅናቄ መደረጉን በመግልጽ ንቅናቄው እስከ ወረዳ ድረስ በማውረድ የሚቀጥል መሆኑን ገልጽዋል። ገልጽዋል።ተማሪዎች በክልሉ ባለው ችግር ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ከትምህርት ገብታቸው እንዳይቀሩ ለማድረግ ከማህበረሰቡ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ከሶስት ሺሕ በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ እየሰሩ አለመሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
በአማራ ክልል ባለዉ የጸጥታ ችግር ምክንያት አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸው ተገለጸ
መጋቢት 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በ2017 ዓ.ም በሶስት ዙር የተማሪዎች ምዝገባ የተካሄደ ሲሆን በተካሄደው ምዝገባም ከሰባት ሚሊዬን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 2.8 ሚሊየን ተማሪዎችን ብቻ መመዝገብ መቻሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።

ምላሽ ይስጡ