በኢትዮጲያ ሜትሮሎጂ ኢኒስቲትዩት የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሳምነዉ ተሾመ በሃገራችን ካሉ 3 ወቅቶች አሁን ያለንበት የበልግ ወቅት በተለይም ሲዳማ፤ ጉጂ እና ቦረናን ጨምሮ በሃገራችን የደቡቡ ክፍል ለሚገኙት አካባቢዎች ዋነኛ የዝናብ ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ የዝናብ ወቅት በሰብልና እንስሳት ጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል፣ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲወሰድ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከ1 ወር በፊት መረጃዎች እንደተሰጣቸው ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ካለፉት 10 ቀናት ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ አካባቢዎች በተለይም በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፤ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች ላይ የተሻለ የዝናብ ተደራሽነት እንዳለና እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ከሜትሮሎጂ ኢኒስቲትዩት በየጊዜው የሚወጡ የአየር ትንበያዎችን በመከታተል በእንስሳትና በሰብል ሊከሰቱ የሚችሉ ተጽዕኖዎችን መከላከል እንደሚገባ አመላክተዋል።
ከሰሞኑ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተው የእንስሳት ወረርሽኝ ከአየር ጠባይ መቀያየር ጋር ተያያዥነት እንዳለው መገለጹ አይዘነጋም።
ምላሽ ይስጡ