በሃረሪ ክልል በስፋት ጅቦችን በማላመድ ለቱሪስት የማስጎብኘት እንቅስቃሴ በቱሪዝም ዘርፉ የሚታወቅ ነው።በልዩ ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃዋሳም ጅቦች በቀን የሚጎበኙበትን ስፍራ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች አሁን ላይ በርካታ ቱሪስቶችን እየሳቡ መሆኑን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት የሃዋሳ ከተማ ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ባለሙያው አቶ ደበበ ዳንኤል ናቸው ።
በሃዋሳ የፍቅር ሃይቅ ዙሪያ የሚገኘው አሞራ ገደል አካባቢ ጅቦቹ ተከልሎ በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ እንዲኖሩ በማድረግና የራሳቸው ጠባቂ በማዘጋጀት ለቱሪስት ምቹ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
አካባቢው የተለያዩ ብርቅዬ እንስሳትንና አእዋፋትን የያዘ መሆኑን የሚያነሱት ባለሙያው አሁን ላይ ጅቦች በቀን የሚጎበኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት በመቻሉ ከተማው በርካታ የሆነ የጎብኚዎችን ቁጥር እያስተናገደ መሆኑንና ያለውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ማነቃቃት መቻሉን አስረድተዋል ።
ባለሙያው አክለውም በቱሪዝም ሚኒስቴር በኩል የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ ከተማውን ለማልማት የተጀመሩና በእቅድ ደረጃ የተያዙ በርካታ ስራዎች መኖራቸውን አንስተው ፤ ያሉትንም የቱሪስት መዳረሻዎችን እሴት ጨምሮ በመስራት የቱሪዝም ፍሰቱን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባም ነው ያመላከቱት ።
ምላሽ ይስጡ