እስከ መስከረም መገባደጃ ያላገቡ ሰራተኞችን ጋብቻ ካልፈጸሙ የስራ ዉል እንደሚያቋርጡ የሚያስፈራራ ፖሊሲ ያስተዋወቀው በቻይና የሚገኝ አንድ ኩባንያ ማሳሰቢያውን አንስቻለሁ ብሏል።
በምስራቅ ቻይና ሻንዶንግ ግዛት የሚገኘው የሹንቲያን ኬሚካል ማቀነባበሪያ ተቋም፤ ባለፈው ወር ለ1 ሺህ 200 ከ28 እስከ 58 እድሜ ክልል ለሚገኙ ያላገቡ ሰራተኞቹ የተፋተቱትን ጨምሮ እሰከ መስከረም 30 እንዲያገቡ የተፋቱት ደግሞ ትዳራቸዉን እንዲያድሱና እንዲያሳዉቁ ማሳሰቢያ ሰጥቶ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ስካይ ኒውስ እንዳለው በፖሊሲዉ ላይ በመጀመሪያው ሩብ አመት ትዳር ካልተፈጸመ ተቋሙ ይታገሳል ግን ምክንያት ሊኖረዉ ይገባል ይላል፤ ሁለተኛው ሩብ ዓመት ካልተጠናቀቀ ኩባንያው ግምገማ ያካሂዳል በሶስተኛው ሩብ አመት ማግባት እና ቤተሰብ መመስረት ካልቻላችሁ ኩባንያው የስራ ውልዎን ያቋርጣል የሚል ነጥብ ይገኝበታል፡፡
ያላገቡ ሰራተኞች ትዳር እንዲመሰርቱ እና ልጅ እንዲወልዱ ለቀረበላቸው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ባለመስጠታቸዉ ለወላጆች ምክር የማይታዘዙ ናቸው ሲል ተቋሙ ወቅሷል።
የቻይና መንግስት በሀገሪቱ እያሽቆለቆለ ያለውን የወሊድ መጠን ለማሳደግ ሰዎች እንዲጋቡ እና ልጆች እንዲወልዱ ለማበረታታት ባደረገው ጥረት መሰረት ተቋሙ ይህን ፖሊሲ ማዉጣቱን ስካይ ኒዉስ ዘግቧል፡፡
ምላሽ ይስጡ