የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መዲናዋ ላይ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ለመቀነስ በ10 የተመረጡ ቦታዎች ላይ የከተማ አውቶቡስ የታክሲ አገልግሎት የሙከራ ስራው ማስጀመሩን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
የከተማ አውቶቡስ ታክሲ በሚል ኮስትር በተሰኙ ተሽከርካሪዎች አገልግሎቱን ካስጀመረ አንድ ወር እንደሆነው የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የቴክኒክ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታምሩ ፉፋ ገልጸዋል።
በድርጅቱ አዲስ አሰራር መሰረት የተጀመረው የታክሲ አገልግሎት የጭነት መጠኑ በወንበር ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በከተማዋ በተመረጡ ቦታዎች ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የተደረጉት ተሽከርካሪዎቹ የተሳፋሪዎቹን ምቾት የሚጠብቁ እንደሆኑ የተገልጸ ሲሆን፤ እንደየ ስምሪታቸው ወጥ ታሪፍ ያላቸው መሆኑን በድርጅቱ የቴክኒክ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታምሩ ፉፋ ተናግረዋል።
የከተማ አውቶብስ ታክሲዎች በሙከራ ጊዜያቸው በሚታየው ውጤት መሰረት አሁን ካሉት አስር ስምሪቶች በተጨማሪ በሌሎች የከተማዋ ክፍሎች የማዳረስ ስራ ሊቀጥል እንደሚችል የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የቴክኒክ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ