መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ለሚደረጉ ምክክሮች ሰላም ትልቁን ድርሻ የያዘ ነው ብለዋል፡፡
በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች ያሉ ታጣቂዎችም ሆኑ መንግስት ሰላምን ለማጽናት ቁርጠኛ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡
አክለውም እንደ ሀገር በሚከሰቱ እና እየተከሰቱ ባሉ ግጭቶች እንዲሁም አለመረጋጋቶች ሳቢያ የንብረት ውድመት፤ የአካል ማጣት በስፋት እየተስተዋለ በመሆኑ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ እንደሚኖርባቸው አስታውቀዋል፡፡
በተለይ የጸጥታ አካላት ሰላም በማስፈኑ ረገድ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡
የህግ ባለሙያው አቶ ሳሙዔል ግርማ፤ ባለፉት ጊዜያት በክልሎቹ ያለው የጸጥታ ችግር ኮሚሽኑ ስራውን በአግባቡ እንዳይሰራ እክል መፍጠሩን ገልጸው፤ በሚቀጥሉት ጊዜያት በተጨመረለት የስራ ጊዜ በሚያንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ሁሉ አስፈላጊው ከለላ እና ጥበቃ እንደሚያሻው አመላክተዋል፡፡
አገራዊ የምክክር ኮምሽኑ በተጨመረለት የ1 ዓመት የስራ ዘመኑ የተሳካ ስራ እንዲሰራ አስፈላጊው ትብብር ሊደረግለት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ