ስደትን ለማስቆምና ከስደት ተመላሾችን ለማቋቋም አጋዥ አካላት እንደሚያስፈልጉ የካርቱም ፕሮሰስ በተሰኘ በስደትና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ የሚሰራ ተቋም ባዘጋጀዉ መድረክ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ህብረት ጉዳዮች ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ሳሙኤል ተናግረዋል።
ካርቱም ፕሮሰስ የተባለዉ ተቋም በአውሮፓና በአፍሪካ ስደትና ከስደት ተመላሾችን በሚመለከት የሚሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ላለፉት አስር አመታት በስደት ተመላሾች ዙሪያ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
አሁን ላይ በተለይም በኢትዮጵያ ወጣቶች እንዳይሰደዱ ከምንጩ ለማድረቅና ለወጣቶች ስራ ለመፍጠር እንደ ሀገር በገንዘብ አቅም ጠንካራ መሆን እንደሚገባ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። እንዲሁም እንደ አፍሪካም ሆነ እንደ ኢትዮጵያ ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም የገንዘብ አቅም ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል።
በመሆኑም ከአጋር አህጉራዊም ሆነ አለም አቀፋዊ ተቋማት ጋር መስራት እንደሚያስፈልግ በመግለጽ የካርቱም ፕሮሰስ አላማም ይሄው መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።
ዛሬ የካቲት 12 ቀን በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የካርቱም ፕሮሰስ በስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አያያዝ ዙሪያ ከተለያዩ ከሚመለከታቸው አለምአቀፍ ተቋማትና አጋር አካላት ጋር በተለይም በጋራ ስደትን ከማስቆምና ተመላሾችን ከማቋቋም አንጻር ስለሚሰራበት ሁኔታ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ምላሽ ይስጡ