የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የቱሪዝም ዘርፉን ያነቃቃ እና ለቀጣይ በዘርፉ አሁን ካለው በበለጠ እንዲሰራ እቅድ የተያዘበት ጭምር መሆኑን የኢትዮጵያ ቱሪዝም እና ሆቴል ገበያ ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 46ተኛው የስራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ በተሳካ መልኩ መካሄዱን የማህበሩ ዳይሬክተር አስማ አመርቱ ተናግረዋል።
ለስብሰባው የመጡ እንግዶች በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን እንደጎበኙ የገለጹት ዳይሬክተሯ አሁንም ለስበሰባው መጥተው ያልተመለሱ እንግዶችን የማስጎብኘት ስራው መቀጠሉን ተናግረዋል።
በሀገሪቱ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች ቢኖሩም በቀጣይ ሀገሪቱን በቱሪዝም ዘርፍ ለማስተዋወቅ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
የቱሪዝም መሰረተ ልማት ማሻሻል በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ማፍራት መዳረሻዎችን ማስተዋወቅና ከሌሎች ሀገራት ጋር በቅንጅት መስራት የሚሉት በቀጣይ የተያዙ እቅዶች መሆናቸውን አመላክተዋል።
እንደ ሀገር የጸጥታው ሁኔታን በማረጋገጥ አሁን ካለው በተሻለ መስራት እንደሚቻልም ገልጸዋል።
38ተኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ እና 46ተኛው የስራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ አዲስ አበባ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ ትልቅ ስኬት መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።
ምላሽ ይስጡ