በየአመቱ የአፍሪካ ህበረት ጉባኤ ሲካሄድ በኔፓድ አስተባባሪነት የሚካሄደው የአቻ ሀገራት ግምገማ ተጠቃሽ ነው፡፡ በግምገማው ፈቃደኛ የሆኑ ሀገራት በመልካም አስተዳደር ፤ በሠላምና ፀጥታ እንዲሁም በፋይናንስ አስተዳደር የሰሩትን ስራ በገለልተኛ አካላት ያስገመግማሉ፤ግብር መለስም ይወስዱበታል ነው የተባለው፡፡
ኢትዮጵያም የአቻ ግምገማ ሰርዓት ከመሰረቱ ሀገራት መካከል ብትሆንም እስካሁን አለመገምገሟ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያን በመወከል #በአፍሪካ_ህብረት ዛሬ በነበረው የግምገማ ሰርዓት ላይ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍፁም አሰፋ በቅርቡ ኢትዮጵያ እራሷ ለማስገምገም ማቀዷን ተናግረዋል፡፡
African Peer Review Mechanism (APRM) የአፍሪካ በ2063 ለመድረስ ላለመው ትልም አቅም የሚፈጥር ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ አንዳንድ ሀገራትም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በግልጽ የሚመለከቱበት ብሎም ከሌሎች ሀገራት ልምድ የሚወስዱበት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በስርዓቱ ምን አይነት ሚናን እየተወጣች ትገኛለች ያልናቸው ሚኒስትሯ፤በቀጣይ በፍቃደኝነት እራሷን ለማስገምገም ዝግጅት እንደምታደርግ አስታዉቀዋል፡፡
አምባሳደር ነብዩ ተድላ በበኩላቸው የአቻ ግምገማ ሰርዓቱ መካሄዱ ህብረቱ ያስቀመጣቸው ግቦች እውን እንዲሆኑ ለማስቻል አይነተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያም በቅርቡ አቻ ግምገማን ታስደርጋለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡
አቻ መገማገሚያ ሰርዓቱ ልክ እንደ አፍሪካ ህብረት ሁሉ የፋይናንስ እጦትና የአፈፃፀም ጉዳይ ትልቅ ትግዳሮት እንደሆነበት ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ