የካቲት 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) 38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በነገው እለት የህብረቱ አባል ሀገራትና የክብር እንግዶች በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ከመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በርካታ ጉባኤዎችም ቀደም ብሎ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በዛሬው እለትም የህብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ መሃመት የታደሙበት የህብረቱ ሀገራት ልምድ የሚለዋወጡበትና ተሞክሮዋቸዉን የሚያጋሩበት እንዲሁም ግምገማ የሚደረግበት ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በጉባኤውም የህብረቱ አባል ሀገራት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ቀጣይነት ያለው እድገትና ሠላምና ፀጥቷ የተረጋገጥች አፍሪካን ለመፍጠር ከንግግር ባሻገር ተጨባጭ ስራዎችን መስራት እንደሚገባቸው ተመላክቷል።
የህብረቱ ዋና ኮሚሽነር ሙሳፋቂ መሃመት የግምገማው ዓላማ እውን እንዲሆንና ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አሁንም የህብረቱ አባላት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።
የፕላና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ፤ ኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ሠላምና ፀጥታ የተረጋገጠባትን አፍሪካ እውን እንዲትሆን በቁርጠኝነት እየሰራች ትገኛለኝ ብለዋል።
ምላሽ ይስጡ