የህብረት ስራ ሸማች ማህበራት አምራቹ ምርቶችን በተገቢው ዋጋ ለገበያ እንዲያቀርብ፤ ሸማቹም አላስፈላጊ በሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይጎዳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የፌደራል የህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ ገልጸዋል፡፡
በሌላው አለም ማህበራቱ በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋ እንደሚያረጋጉ የገለጹት ኃላፊው፤ እንደሃገር ግን ያለውን አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ውጤታማ ስራ አለመሰራቱን ነው ያብራሩት፡፡
የህብረት ስራ ሸማች ማህበራት በሌሎች አዳጊ ሃገራት የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ ገና በርካታ ስራ ይቀረናል የሚሉት ኃላፊው፤ አሁን ያሉት 110 ሺ የህብረት ስራ ማህበራት ያላቸው ካፒታልና አቅም ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካለችበት የልማት ጉዞ አንፃር የማይመጥንና አስተኛ ነው ሲሉ አመላክተዋል።
ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ስራ ኮሚሽን ከፌደራል የህብረት ስራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የክልል አምራችና ፋብሪካዎች ለከተማዋ ነዋሪዎች ምርቶችን በቀጥታ እንዲያቀርቡ የሚያደርግ የባዛር ገበያን በኤግዚቪሽን ማዕከል በመክፈት ማስተዋወቁ የሚታወቅ ነው።
ምላሽ ይስጡ