በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ሰዓት ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት፣በክልሉ የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ከነገ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
በለውጡ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የስራ ሰዓት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ተኩል እንደሚሆን አስታውቀዋል።
እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከዘጠኝ ሰዓት እስከ 11 ተኩል የነበረው ከአስር ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ተኩል እንዲሆን መወሰኑን አቶ ኡቶው አመልክተዋል።
የስራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሺና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር አስረድተዋል።
ምላሽ ይስጡ