በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ላይ በተደረገ ጥናት በአከባቢው የሜርኩሪ መርዛማ ኬሚካል አጠቃቀም ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ መሆኑን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት በትግራይ ክልል የመሬት እና ማእድን ቢሮ ዳይሬክተሩ አቶ ፍሰሃ ግርማይ ናቸው፡፡
በክልሉ በማእድን ማውጣት ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎች የሚጠቀሙት ሜርኩሪ ለተለያዩ የመተንፈሻ አካል ህመሞች እንደሚያጋልጥ፤ በተለይም ህፃናትና ነፍሰ-ጡሮች ላይ ካንሰር ሊያስከትል እንደሚችል በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡
ችግሩ ከዚህም ባለፈ በረጅም ጊዜ ሒደት በዘር ለሚተላለፍ የጤና ጉዳት እንደሚያደርስ አስታውቀዋል፡፡ አሁን ላይ በአካባቢው ያሉ እንስሳቶች፣ ሰብሎች እና ነዋሪዎችን እየጎዳ እንዳለም ገልጸዋል፡፡
የትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ሜርኩሪን የሚጠቀም ብቸኛው ክልል መሆኑን ያረጋገጠው ጥናቱ አሁን ላይ እያደረሰ ካለው ተጽዕኖ አንጻር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተመላክቷል ብለዋል። እንደ ሲያናይድ፣ ሜርኩሪና አርሰኒክ የመሳሰሉ መርዛማ ኬሚካሎች ለማእድን ማውጣት ስራ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ያስታወቁት ዳይሬክተሩ፤ በዚህ የተነሳ ስነ ምህዳሩ፤ አየሩ እና የማህበረሰቡ ጤና ጉዳት እየደረሰበት ነው ብለዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ