እንደ ሀገር የፀጥታ ችግርና ካሳ ክፍያ የመንገድ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ማድረጉን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ተቋሙ የተበላሹ መንገዶችና አዳዲስ የመንግድ ግንባታዎች እያከናወነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንግዶች አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ አስራት አሳሌ ተናግረዋል፡፡
መንገዶቹን በፍጥነት በመስራት ለተጠቃሚ እንዳይደርስ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን አቶ አስራት ገልጸዋል፡፡
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ችግሮቹን ለመፍታት ቢሞከርም በፍጥነት እልባት ባለማግኘታቸው አብዛኛዎቹ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንዲጓተቱ እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወጪ በማድረግ የመንገድ ጥገናዎች እያከናወነ ቢሆንም በግንዛቤ እጥረትና ህግን ባለማክበር ዳግም የሚበላሹበት ሁኔታ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
በተለይም አብዛኛዎቹ ከባድ አስከርካሪዎች ከተፈቀደላቸው ጭነት በላይ በመጫን መንገዱ ዳግም እንዲበላሽ ያደርጋሉ፤ በዚህም ተጠቃሚዎች እና መንግስት ለከፍተኛ ኪሳራ እንደሚዳርግ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በስድስት ወሩ ከሶስት መቶ ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ የመንገድ ግንባታ ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ