የአገው ፈረሰኞች ማህበር ዓመታዊ በዓል ከ4 ሺህ 500 በላይ ፈረሰኞች እና ከ500 በላይ እግረኞች እንዲሁም የክብር እንግዶች በተገኙበት ዘንድሮ ለ85ኛ ጊዜ በእንጂባራ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን ማህበሩ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታዉቋል፡፡
በዓሉ ከዚህ ቀደም ከነበረው ይበልጥ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር፣ ሰፊ ዘግጅት መደረጉን የገለጹት የአገው ፈረሰኞች ማህበር ሊቀመንበር አለቃ ጥላዬ አየነው፤ከዚህ በፊት የነበረው የበዓሉ አከባበር የፈረሰኞች እና የማህበሩ ብቻ ተደርጎ የሚሰወድ እንደነበር ጠቅሰው አሁን ላይ ህዝቡ በእኔነት ስሜት እያከበረ እና እየተሳተፉበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ አስተዳደር የሚመራ ከህዝቡ እና ከፈረሰኛ ማህበሩ የተወጣጣ አብይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ለበዓሉ አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ ተጠናቅቆ የበዓሉን ቀን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ነው ሊቀመንበሩ ያመላከቱት፡፡
ከእንጂባራ ውጭ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ የዞኑ ተወላጆችም በዓሉን እንደሚያከብሩ የጠቆሙት የማህበሩ ሊቀመንበር አለቃ ጥላዬ አየነው በዓሉን ለማክበር እና ለመታደም እንዲሁም ለማወቅ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ክፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ማህበሩ ከየትኛውም የፖለቲካ እና መሰል እንቅቀስቃሴች ነጻ በመሆኑ በተለይ የበዓሉ አከባበር አባቶች በአደዋ ጦርነት፣ በፈረስ ወጥተው ድል ያደረጉበት ታሪክ የሚውሳበት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ህዝቡ የበዓሉ ባለቤት በመሆኑ በሰላም ተከብሮ እንዲውል የዞኑ ህዝብ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በዓሉ በሰላም ተክብሮ እንዲጠናቀቅ፣ ከዞኑ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመሆን በቂ ቅድመ ዘግጅት መደረጉን አንስተው፣ በበዓሉ አከባባር ላይ ምንም አይነት የጸጥታ ስጋት እንደሌለም ተናግረዋል፡፡
85ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል የፊታችን ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በእንጂባራ ከተማ ሺህዎች የሚቆጠሩ ፈረሰኞች፣ እና ተጋባዥ እንግድች በተገኙበት ይከበራል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ