የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን፤ ብቁ የትምህርት ደረጃ እና የስነ አመራር ችሎታ ያላቸው የአመራር እርከን ቢሰጣቸው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት የሚችሉ ሴቶች እያሉ ከወንዶች እኩል እድል እየተሰጣቸው አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፤ ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮም ባለፉት ጊዜያት ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት ከበርካታ ቢሮዎች ጋር በጋራ ሲሰራ እንደቆየ ነው ያስታወቁት፡፡
አሁንም ያለው የሴቶቸ ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ፤ በቀጣይ የአመራሩ ዘርፍ ሴቶችን ያማከለ እንዲሆን ቢሮው በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የሴቶችን ንቁ ተሳትፎ ለማሳደግ በሚሰራው ስራ በተለይም ከአረብ ሃገራት ተመልሰው ለመጡ ሴቶች የስነ ልቦና፣ የጤና ብሎም የስራ ፈጠራ ስልጠና ለመስጠት ከፍተኛ በጀት በማዘጋጀት ከተለያዩ ተቋማት እና በጎ ፈቃደኛ ማህበራት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ