ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቀጣይ አመት በሚካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በተወሰነ መልኩ የምርጫ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ቦርድ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ቦርዱ ይህን የገለፀው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር ባደረገበት ወቅት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሐይሉ፤ ቦርዱ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ በኋላ ከዚህ ቀደም የነበረው አዋጅ 1162/2011 ክፍተቶች የታዩበት በመሆኑ በአዲስ መልኩ ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከዚህ ቀደም ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር ምክክር መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡ አሁን ደግሞ ከሲቪል ማህበራት ድርጅቶችና ከመገናኛ ብዙሀን ባለሞያዎች ጋር ምክክር መደረጉን አመላክተዋል፡፡
በምክክር መድረኮቹ ተሳታፊ አካላት ማሻሻያ በተደረገበት አዋጅ ላይ ግብአት ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ሀሳቦችን እንዳንጸባረቁም ተናግረዋል፡፡
ከማሻሻያው አንዱ የምርጫ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እንዲደረግ የሚል ሲሆን ይህም ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በተወሰነ መልኩ በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች በአስገዳጀነት ሴቶችን ተሳታፊ እንዲያደርጉ፤ ነፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲያገኙ፤ ፓርቲዎቹ ጥፋት ከተገኘባቸው ከዚህ ቀደም ማስወገድ የሚለውን በመቀየር ለአምስት አመት ታግደው እንዲቆዩ የሚለው እንዲሁም ከምርጫ በኋላ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በምክክር እንዲፈታ የሚሉ ሀሳቦች በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ከተካተቱት መካከል እንደሚጠቀሱ ተገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ