ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ‘’ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለው’’ በሚል ሃሳብ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያና በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የተሰበሰበ ገቢ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መሰጠቱ ተገለጸ፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፉት 19 አመታት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የበጎ አድራጎት ስራ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በዘንድሮው የበጎ አድርጎት ዘመቻ 3 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ ለአዲስ ህይወት አይነ ስውራን ማዕከል፤ለአረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ ሰጪ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ህብረት እንዲሁም ለቪዥን ማየት የተሳናቸው ህጻናት ወላጆች የበጎ አድራጎት ድርጅት ለእያንዳንዱ ድርጅት የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መደገፍና በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶችን ማጠናከር ከሁሉም የሚጠበቅ ሃላፊነት እንደሆነ የገለጹት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሴቶችና ህጻናት ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የመሆን እድላቸው ሰፊ በመሆኑ ይህንን ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው አካል ጉዳተኛ ሴቶችና ህጻናትን የሚደግፉ ድርጅቶችን ለማጠናከርና ለመደገፍ እንዲያስችልም ከሌሎች ድርጅት(ተቋማት) ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ ከተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች እስካሁን ባለው ጊዜ ከ 35 ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ ለህጻናት ፤ ለሴቶች፤ለአካል ጉዳተኞች ብሎም ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንና ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
011-639-28-52
011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
#ማህበራዊ#ሴቶች#ማህበራዊ#ጉዳይ#ሚኒስትር#ሚኒስቴር#ethiopia#addisababa#menahria#menahria_radio
ምላሽ ይስጡ