ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ1446ኛው የሃጅ እና ዑምራ ጉዞ ምዝገባ ከዛሬ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መግለጹን ተከትሎ ዋጋዉ የተጋነነ መሆኑን ያነጋገርናቸዉ የእምነቱ ተከታዮች ገልጸዋል፡፡
የዘንድሮ የሐጅ እና ዑምራ የጉዞ ዋጋ 625 ሺህ ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የታየው የዶላር ጭማሪና በአየር መንገዶች ላይ ያለው የትኬት ዋጋ መናር ዋጋው ከፍ እንዲል እንዳደረገው ቢገለጽም የማህበረሰቡን አቅም ያማከለ ዋጋ አለመሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃጅ እና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ መሀመድ እንደተናገሩት ለሃጅ ተጓዞች የተተመነዉ ዋጋ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የአገልግሎት ዋጋን በመቀነስ፤ በዕቅድ የተያዙ ፕሮጀክቶችን በማጠፍና በሳውዲ የሚቀርበውን አገልግሎት ተመጣጣኝ እንዲሆን በማድረግ 108 ሺህ ብር ቅናሽ ተደርጎ ጭምር ስለተሰራ እንጂ 730ሺህ ብር ይሆን ነበር ሲሉ አብራርተዋል፡፡
አሁን የተቀመጠዉም ተመን ተጓዦቹ ሄደዉ የሚያገኙት አገልግሎት ጋር ተሰልቶ የተቀመጠ እንጂ ዋጋ ለማስወደድ የተሰላ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉ በጭማሪ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ሃላፊዉ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ ሃገራት ያሉ የእምነቱ ተከታዮች አቅም ለሌላቸዉ ተጓዞች ወጪያቸዉን እንደሚሸፈፍኑ በየአመቱ ይገለጻል ፤በዚህ አመት ምን ያህል ተጓዞች በዚህ እድል ተጠቃሚ ናቸዉ የሚለዉን መናኸሪያ ሬዲዮ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ፤እገዛ ተደርጎላቸዉ ስለሚጓዙ ተጓዞች መረጃዉ የለኝም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ላይ ለአስር ሺህ ሰዎች የጉዞ ፍቃድ እንደሚኖር ተጠቁሟል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
011-639-28-52
011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
Like
Comment
Send
Share
ምላሽ ይስጡ