በተጨማሪም በሐረር ከተማ ዛሬ ሌሊት 8፡00 ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ነው የተባለው
በደብረ ብርሀን ከተማ በደረሰ የእሳት እንዲሁም በሐረር ከተማ እና በስልጤ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ፡፡
በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ አደጋው ዛሬ ከጠዋቱ 3፡30 በወረዳው ሌፎ በሚባል አካባቢ ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ከባጃጅ ጋር በመጋጨቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የእሳት አደጋው በደብረብርሀን ከተማ አየር ሀይል ቀበሌ ትናንት ምሽት 2፡30 የደረሰ ሲሆን የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
የከተማው ፖሊስ መምሪያ፤ የእሳት አደጋው የተነሳው ከመኖሪያ ቤት መሆኑንና በቤት ውስጥ ቤንዚን መኖሩ አደጋውን አባብሶ ለመቆጣጠር አዳጋች እንዳደረገው ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል በሐረር ከተማ ዛሬ ሌሊት 8፡00 ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
አደጋው የደረሰው በሬ የጫነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪን ለማዳን ሲሞክር በመገልበጡ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በአደጋውም በአይሱዙ ተሽከርካሪ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንና በአይሱዙ ተሽከርካሪ ላይ ከተጫኑት 15 በሬዎች መካከልም ሶስቱ መሞታቸው ተገልጿል፡፡
የአይሱዙ አሽከርካሪው ለጊዜው መሰወሩን ጠቁመው፤ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ኢዜአ እና ፋሚኮ ዘግበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
011-639-28-52
011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ