ጥር 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያና አርጀንቲና በአየር አገልግሎት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግሥቴ እና የአርጀንቲና አየር ትራንስፖርት ዘርፍ ዋና ጸሃፊ ፍራንኮ ሞጌታ ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመንገደኛ እና የጭነት በረራ አገልግሎት ከኢትዮጰያና አርጀንቲና መዳረሻ ጣቢያዎች ባሻገር በአርጀንቲና ግዛት ውስጥ እንዲሁም ወደየትኛውም 3ኛ አገር መዳረሻ ጣቢያ መብረር እንዲችል የሚፈቅድ ከአየር ትራፊክ መብት አንጻር ሲታይ ሁሉንም የትራፊክ መብቶች የፈቀደና ገበያው በፈቀደ ልክ ያለምንም ገደብ በማንኛውም የአውሮፕላን ዓይነት የበረራ ምልልስ የማድረግ መብት የሚያጎናፅፍ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በተመሳሳይ መደበኛ ያልሆኑና የቻርተር በረራዎች ያለገደብ መብረር የሚያስችል መብት የሚሰጥ ነው፤ ስምምነቱ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎትን ከማስፋፋት አንጻር የዓለማቀፍ መዳረሻዎችን ቁጥር የሚያሳድግ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራንስፖርቱ ያለውን የገበያ ድርሻና ተወዳዳሪነት (Competitive Advantage) የሚያጠናክር መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
ስምምነቱ መንገደኛና ጭነትን ከማጓጓዝ ባሻገር የሁለቱን ሀገራት የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍሰት ለማበረታታትና ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ለመረዳት ተችሏል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ