ቴል አቪቭ በጋዛ ሃማስ ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማቆም እና እስረኞችን ለመፍታት እንዲሁም፣ ታጣቂ ቡድኑ ታጋቾችን ለመልቀቅ፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና/ አስታራቂው የኳታሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ቢን አብዱራህማን አልታኒ ይፋ ማድረጋቸውን ይታወቃል።
በዚህም ለ6 ሳምንታት የሚቆየው/ የመጀመሪያው ምዕራፍ/ የተኩስ አቁም፣ የፊታችን ከፈረንጆቹ ጥር 19 ጀምሮ፣ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተገልጿል።
ምንም እንኳን፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና፣ የኳታሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሃመድ፣ ሁለቱ አካለት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ቢገልጹም፣ ይህ ዘገባ እሰከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ ፊርማቸውን አላኖሩም፡፡
የኳታሩ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ተግባራዊነቱ፣ እሁድ እንደሚጀመር ቢናገሩም፣ ስምምነቱ አሁንም የእስራኤል ካቢኔን ይሁንታ ይጠይቃል ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት፣ ሃማስ ሁሉንም የስምምነት ክፍሎች መቀበሉን አስታራቂዎቹ፣ ኳታር እና አሜሪካ፣ ለእስራኤል እስካላሳወቁ ድረስ ካቢኔው እንደማይሰባሰብ አስታውቋል።
በዚህም ከትላንት ማለዳ ጀምሮ፣ ስብሰባ ይቀመጣል የተባለው ካቢነው፣ ይህ ዘገባ እሰከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ስብሰባው አለመካሄዱን ቢቢሲ ዘግቧል።
ይህን ርዕሰ ጉዳይ በትንታኔ ተመልክተነዋል 👉 https://youtu.be/QrWOz5OjpDc
ምላሽ ይስጡ