ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተለያዩ መንገዶች የጥምቀት በዓል አላማን የማያንጸባርቁ ድርጊቶችን መፈጸም እንደማይቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ክብረ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቀ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀናጀ ፍተሻ እንደሚደረግ ገልጸው፤ በበዓሉ ሰላማዊ ሒደት ላይ ስጋት የሚደቅኑ ቁሳቁሶችን ህዝብ በተሰበሰበት ቦታ ይዞ መገኘት እንደማይገባም ተናግረዋል፡፡
በጥምቀት በዓል ዜጎች የተለያዩ አልባሳት የሚጠቀሙ ቢሆንም፤ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክት የሚያስተላልፉ ጽሑፎች ያሉባቸውን አልባሳት መጠቀም እና እውቅና የሌላቸው አርማዎችን ይዞ መገኘት የማይቻልና ፤ ወንጀል በመሆኑ በጸጥታ ሃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
በማህበራዊ የትስስር ገጾችም ድብቅ ዓላማ በመያዝ ለህብረተሰቡ የተዛባ መልክት ከማስተላለፍ መቆጠብ እንደሚገባ ነው ምክትል ኮማንደሩ የገለጹት።
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ማህበረሰቡ የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ጠይቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ