ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በ9ኙ ክፍለከተሞች በተመረጡ ቦታዎች በተካሄደ ቁጥጥር የአልኮል ትንፋሽ ምርመራ ከተደረገላቸው 1 ሺ 831 አሽከርካሪዎች ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት ከመጠን በላይ ጠጥተው ሲያሽከረክሩ መገኘታቸው የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የገናን በዓል አስመልክቶ በልዩ ሁኔታ ባካሄደው ቁጥጥር 53 አሽከርካሪዎች ከከተቀመጠው መጠን በላይ ጠጥተው ሲያሽከረክሩ እንደተገኙ እና 60 አሽርካሪዎች አልኮል ጠጥተው ሲያሽከረክሩ መገኘታቸውን የቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ዲባባ ተናግረዋል፡፡
የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠበር በወጣው ደንብ 557/2016 መሰረት አሽከርካሪዎች የገንዘብ ቅጣት እንደተቀጡ ዳይሬክተሯ አንስተው በከተማዋ የትራፊክ አደጋ መንስኤ ተብሎ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ጠጥቶ ማሽከርከር አንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በሁሉም ክፍለከተማ የአልኮል መለኪያ መሳሪያ ቢኖርም ካለው የተሽከርካሪ መጠን ጋር ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአሁኑ ወቅት ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ጥኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ዳይሬክተሯ አንስተው በመጪው ጥቀምቀት በዓልም ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ የመንገድ ትራፊክ ፍሰት ሰላማዊ አንዲሆንና የትራፊክ አደጋንም አስቀድሞ ለመከላክል ተቋሙ የሚያደርገውን ጥረት አሽከርካሪዎች ደንብና ህግን አክብረው በማሽከርከር እንዲያግዙ ዳይሬክተሯ ጥሪ ቀርቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ