ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የትርፋማነት እና ይዘት ክፍፍል በተለይ ደግሞ ወጪ እና ገቢያቸውን በማያመጣጥኑ ክለቦች ላይ ፕሪሚየር ሊጉ የነጥብ ቅጣት ሲያስተላልፍ መቆየቱ አይዘነጋም።
የፕሪሚየር ሊጉ በ3 አመት ውስጥ ከ105 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ አንድ ክለብ ወጪ እንዲያደርግ የማይፈቅድ ወይም ደግሞ ከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን በላይ ወጪ እንዳያደርግ ህግ መደንገጉ አይዘነጋም። ታዲያ ከዛ ህግ ጋር የተጣረሰ ጉዞን ተጉዘዋል ያላቸው ኖቲንጋም ፎረስት እና ኤቨርተን ላይ የ4 ነጥብ ቅነሳ እንዳስከተለባቸው የሚታወስ ነው።
ታዲያ ቼልሲ ፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ፤ ሌስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ለቅጣት ከጫፍ ደርሰው ግን እንደምንም ወጪያቸውን በማመጣጠናቸው ከቅጣት መትረፋቸውን ፕሪሚየር ሊጉ አሳውቋል።
ፕሪሚየር ሊጉ በትልቅ ባለሀብት ስር የማይገኙ ክለቦችን ከስር ከስር እየቀጣ በትልቅ ባለሀብት ስር የሚገኙ ክለቦችን ግን እቅፍ-ድግፍ ማድረጉ በብዙዎች ቁጣን ያስነሳ እና ኢ-ፍትሀዊ አሰራር በማለት ፕሪሚየር ሊጉን እንዲተቹት እያስገደዳቸው ይገኛል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ