ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ 15ኛውን አለም አቀፍ የጥናት እና ምርምር ጉባኤ በዛሬው እለት በይፋ አስጀምረዋል።
ጉባኤው ከምልክት ቋንቋ ጋር የተያያዙ በአለም ላይ የሚደረጉ ምርምሮች፤ የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም ወጣት እና አዳዲስ ተመራማሪዎችን ለማበረታት የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አሳልፈው አህመዲን ናቸው፡፡
ጉባኤው በተለያዩ ሀገራት ሲካሄድ መቆየቱን ያስታወሱት መሪ ስራ አስፈጻሚው፤ ኢትዮጵያም የጉባኤው አዘጋጅ እንድትሆን በአለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ መመረጧን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መስማት የተሳናቸው የምልክት ቋንቋ ተናጋሪዎች ቁጥር ከ3 ሚሊየን በላይ እንደሚገመት ያስታወቁት መሪ ስራ አስፈጻሚው፤ የምልክት ቋንቋ ተናጋሪዎች በዕለት ተዕለት የኑሮ ውጣ ውረድ የሚገጥሟቸው ችግሮችን በመለየት መፍትሄ የሚፈለግበት ጉባኤ መሆኑን መሪ ስራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።
ከዚህ በፊት በተካሄዱት ጉባኤዎች በርካታ የምልክት ቋንቋ ተናጋሪ ችግሮችን መቀረፋቸውንም አመላከተዋል።
በቀጣይም የቋንቋውን ተቀባይነት በማሳደግ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ፣ የኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲኖረው ማድረግ የጉባኤው አላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምልክት ቋንቋ እና መስማት የተሳናቸው በሚል በዲግሪ መርሃ ግብር እንደሚያሰለጥን ተገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ