ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር እያካሄደችው ያለው ግንኙነት የባህር በር ለማግኘት የተሻለ ዲፕሎማሲያዊ ሂደት መሆኑን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ከሶማሊያ ጋር እያካሄደችው ያለው ግንኙነት የተሻለ እና የሚመረጥ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ነዉ ሲሉ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ዶክተር አብዱ ሞሐመድ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ከባህር በር ጥያቄ ጋር በተገናኘም ከየትኛዉ ወገን ጋር ስምምነት ማድረግ ለኢትዮጵያ ይበጃል የሚለዉን ለማጤን ምቹ መንገድ ነዉ ብለዋል።
ሀገራት ለዘርፈ ብዙ ጥቅማቸው አንድ ቦታ ላይ ብቻ በቃኝ የሚሉበት ሂደት አይኖርም ሲሉም የገለጹት ዶክተር አብዱ፤ ከሶማሊያ መንግስት ጋር ያለው አዲስ ግንኙነት ሞቃዲሾ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ዳግም በስፍራው መቆየትም ትልቅ ተስፋን ይዞ የሚመጣ ነው ሲሉም አክለዋል።
ኢትዮጵያ እያደረገች የምትገኘው ከሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት ጋር የተቋረጠውን ዲፕሎማሲ ማስቀጠል ነው ሲሉ ሃሳባቸውን የገለጹት ደግሞ የዲፕሎማሲ ባለሞያው አቶ በፍቃዱ ዳባ ናቸው። የአንካራው ስምምነት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ የሚያደርግ ሳይሆን የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው የሚሉት የዲፕሎማሲ ባለሙያው በሁለቱም ወገን አሸናፊነት ያለው ቅርርብ ነው እየተካሄደ ያለው ሲሉ ገልጸዋል።
በተለይም የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል በስፍራው እንዲቆይ ለማስቻልና የቀጠናውን ሰላም በማስከበር ሚናው እንዲቀጥል ለማድረግም አሁን ያለው የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ብዙ ተስፋ ሰጪ ነገሮች አሉት ሲሉ አቶ በፍቃዱ ገልጸዋል።
ከሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር ያለው አዲሱ ቅርርብ ቀጠናዊ ውጥረቶችን ከማርገብም አልፎ በዚያ አካባቢ ላይ ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት ይበልጥ ለማሳካት አማራጭ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ነው ሲሉም ባለሙያው ተናግረዋል።
ከአንካራው ስምምነት በኋላ ኢትዮጵያና ሶማሊያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በርካታ ግንኙነቶችን በተከታታይ እያደረጉ መሆናቸዉ ይታወቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ