ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ17 አመቱ ፓራጓዊ ዲዬጎ ሊዮን ክለቡን በመልቀቅ ሴሮ ፖርቴኖን በመልቀቅ ፊርማውን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለማስቀመጥ ወደ እንግሊዝ በማቅናት ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ጠቁመዋል።
ይሄ ቦታ በዩናይትድ ቤት ላለፉት ጥቂት አመታት ክፍት የነበረ ቦታ ነው ቢባል ብዙ ማጋነን አይሆንም። እዚ ቦታ ላይ የነበሩ ተጫዋቾች በዋናነት በጉዳት ምክንያት ሲቀጥል የጥራት ችግር በዋናነት ይታይባቸዋል። ሩበን አሞሪም ከመጣ በኋላም ያለ ቦታው ዲዬጎ ዳሎን በግራ መስመር ተመላላሽ ቦታ ላይ ሲያሰልፈው መቆየቱ አይዘነጋም።
ታዲያ ይሄንን ቦታ ለመተካት ገበያው ላይ ተጫዋቾችን ለመግዛት እንደሚያማትሩ ሲገለፆ መቆየቱ አይዘነጋም። ታዲያ ዲዬጎ ሊዮን የመጀመሪያ ፈራሚያቸው መሆኑ እንደማይቀር እየተገለፀ ይገኛል። ለዚህ ተጫዋች ወደ 6 ሚሊዮን ፓውንድ ጥቅማጥሙን ጨምሮ ወጪ ያደርጋሉ ተብሎ ይገመታል።
ተጫዋቹ የዩናይትድ ተጫዋች መሆኑ ይረጋገጣል እንጂ ስብስቡን አይቀላቀልም። ስብስቡን የሚቀላቀለው 18 አመት ሲሞላው ነው። ስለዚህ የጤና ምርመራውን አከናውኖ በክለቡ በድጋሜ በውሰት ቆይታ ያደርጋል። በክረምት ማለትም የፊታችን ሀምሌ ወር ላይ ግን የዩናይትድን ስብስብ በይፋ የሚቀላቀል ይሆናል።
ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ኸግን ተከተው የመጡት የፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ የተጫዋች ግዢ ይህ ፓራጓዊ የግራ መስመር ተመላላሽ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ዲዬጎ ሊዮን እንደሚሆ በስፋት እየተዘገበ ይገኛል።
በሚካኤል ደጀኔ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ