👉እሳቱ ዛሬም ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ እንደቀጠለ ነው ተብሏል፡፡
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ በተከሰተው ሰደድ እሳት አማካኝነት የሟቾች ቁጥር ከ24 ማለፉ ተገልጿል፡፡
ሰደድ እሳቱ ወደተለያዩ አካባቢዎች እየተስፋፋ በቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ንብረቶችን ወደ አመድነት መቀየሩን ቀጥሏል፤ የሰዎችን ህይወትንም እየቀጠፈ ነው ተብሏል።
በሰደድ እሳቱ እስካሁን #የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን፤ #ከ137 ሺህ በላይ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል ተብሏል።
ከ12 ሺህ በላይ ትላለቅ መኖሪያ ቤቶችን፣ ህንጻዎችን እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ሙሉ ለሙሉ ማውደሙም ተገልጿል፡፡
በካሊፎርኒያ ባለው ሳንታ ሞኒካ ተራራ መነሻውን ያደረገው ሰደድ እሳቱ በአካባቢው ያለው ከፍተኛ ንፋሳማ የአየር ሁኔታ ሰደድ እሳቱ ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆን አድርጎታል ነው የተባለው።
እሳቱን ለማጥፋት ከ14 ሺህ በላይ የእሳት አደጋ ሠራተኞች በ84 አውሮፕላኖች በመታገዝ ርብርብ እያደረጉ ቢሆንም እስካሁን ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት አልተቻልም ነው የተባለው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ