ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ ገጠራማ የሃገሪቱ ክፍሎች ለአገልግሎት ማስፋፊያ ስራ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንሚያስፈልግ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዛሬው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ 500 ከተሞችን የ4ጂ አገልግሎት፤ 15 ተጨማሪ ከተሞችን ደግሞ የ5ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም በገጠራማ አካባቢዎች የአገልግሎት ተደራሽነትን በማሳደግ በገጠር እና በከተሞች መካከል ያለውን የዲጂታል ክፍተት ለማጥበብ እንደሚሰራ ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡
በገጠር 496 ጣቢያዎችን ለማስፋፋት እንዲሁም ለ1ሺ የገጠር ቀበሌዎች የኔትወርክ ሽፋንን ተደራሽ ለማድረግ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ 90 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ተቋሙ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የቴሌኮም መሳሪያዎችን ለግለሰብ እና ድርጅቶች ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አክለው ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ