ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገራዊ ምክክሩ የአጀንዳ ልየታ ወቅት በተሳታፊዎች የሚነገሩ ጉዳዮችን እንደ አጀንዳ በመውሰድ ማሰራጨት እንደማይገባ የገለጸው የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ፤ ሀገራዊ ምክክር ያስፈለገበት ምክንያት የትኛውም ጉዳይ ቀርቦ ለመነጋገር እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ሲል ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ፤በአጀንዳ ልየታው የሚሳተፉ አካላት አጀንዳ ጠቋሚ ወይም አጀንዳ የሚመስሉ ቀስቃሽ ነገሮችን ሊናገሩ ይችላሉ፤ ይህም መብት ነው ብለዋል፡፡
ማንኛውም ግለሰብ አጀንዳ የመሰለውን ነገር በግሉም፤ በተቋምም ይሁን ባሉ አደረጃጀቶች አማካይነት ማቅረብ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
ይህን መነሻ በማድረግ ያልተገቡ መረጃዎችን ላልተገባ አላማ ማራገብ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ አጀንዳዎቹ ተለይተው ለውይይት ባልቀረቡበት ሁኔታ ድምዳሜ ላይ መድረስ ስህተት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የስነ-አመራር መምህር እና ፖለቲከኛ አቶ ጌትዬ ትርፌ በበኩላቸው፤ የሀገርን ስብራት ለመጠገን በሚደረገው ጥረት ውስጥ የምክክር ሒደቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎባቸው መዘገብ እንደሚገባው በማመላከት ለህዝቡ ሲሰራጩ ወቅትና ጊዜን ማገናዘብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
አሁን ላይ ሀገር በሀገራዊ ምክክርና በሽግግር ፍትህ ትታከማለች ተብሎ በብዙዎች ዘንድ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡ ህዝቡ ጋር የሚደርሱ መረጃዎችን የመመርመርና የማጣራት ልምድ አነስተኛ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄዎች ሊወሰዱ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
ተሳታፊዎችም ቢሆኑ የሚወስኑት ውሳኔ ሀገራዊ እጣፋንታ ላይ እንደመሆኑ ነገሮችን በጥልቀት መመለከት እንደሚገባቸው አስረድተዋል፡፡
የህግ ባለሙያ አቶ አንዷልም በእውቀት በበኩላቸው አንድን አጀንዳ ብቻ መዞ በማውጣት ማራገቡ አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡ እንደ ሀገር ባልተግባባንባቸው ጉዳዮች ላይ ለመግባባት ሲባል ሀገራዊ ምክክር ማስፈለጉን በማመላከት የሚወጡ አጀንዳዎችን የፖለቲካ መታጊያ ያደረጉ ወገኖች አሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እስካሁን በ10 ክልሎች እና 2 ከተማ መስተዳድሮች ከ1 ሺህ 350 ወረዳዎች አጀንዳ የተቀበለ ሲሆን፤ የአጀንዳ ልየታ በተደረገባቸው አከባቢዎች ሁሉ የተነሱ ጉዳዮች ሀገር የሚያፀኑ ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ