ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በዘመቻ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
ከ2011 እስከ 2016 ዓ.ም ከ145ሺህ 250 በላይ 14 ዓመት የሞላቸው ሴት ልጆች ክትባቱን እንዳገኙ የሚናገሩት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ፤ ዘንድሮ ከ9 እስከ 14 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 177 ሺህ 933 ለሚሆኑ ሴት ልጆችን የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ለመስጠት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
በዘመቻው 385 የክትባት ቡድን የተደራጀ ሲሆን 1 ሺህ 524 የጤና ባለሙያዎች እንደሚሳተፉበት ሃላፊው አንስተው በጎዳና ላይ ያሉ ህፃናትም እንደሚከተቡ ገልፀዋል፡፡
ክትባቱን ይሰጣቸዋል ተብሎ የሚጠበቁ ታዳጊ ሴቶች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት በትምህርት ቤት ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ተናግረዋል፡፡
በመዲናዋ በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በሙሉ ክትባቱን ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ሃለፊው አንስተው የተገላጭነት ጥርጣሪ ከሌለ ክትባቱት በህይወት ዘመን ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጥ መሆኑን በመጥቀስ የመለየት ስራዎችን በተማሪዎች እና በወላጆች በኩል እንደሚከናወን አስረድተዋል፡፡
በወላጆችና አሳዳጊዎች በኩል የግንዛቤ ክፍተት መኖሩን የተናገሩት ሃላፊዎቹ በተለያዩ አካባቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራም በቢሮዎቹ በኩል እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ