ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ነዋሪዎች እየገቡባቸው ባሉ አዳዲስ መንደሮች ላይ ተጨማሪ 36 የቅዳሜና እሁድ ገበያ ሊጀመር እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የቅዳሜና እሁድ ሰንበት ገበያዎች የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የተረጋጋ ገበያ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እየተወጡ እንደሆነ የሚናገሩት የቢሮው የገበያ መረጃ ጥናት እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ሙሰማ ጀማል፤በአሁኑ ወቅት ነዋሪዎች በስፋት እየገቡባቸው ባሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ላይ ተጨማሪ 36 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን ለማስጀመር ቢሮው በስራ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመዲናይቱ በአሁኑ ወቅት በተጠናከረ መልኩ 193 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እየሰሩ መሆኑን አንስተው ለተጨማሪዎቹ 36 የቅደሜ እና እሁድ ገበያዎች የሚሆን ቦታ እየተመረጠ መሆኑንና በንግዱ ላይ የሚሳተፉ አቅራቢዎችን በመለየት ስራውን ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቅዳሜና እሁድ ገበያ ላይ ህብረተሰቡ የሰብል ምርቶች እንዲቀርቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረቡን የሚናገሩት ዳይሬክተሩ ከህብረት ስራ ማህበርና ከአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን ምርቶቹን ለማቅረብ በጋራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በገበያዎቹ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 13 የስልክ መስመሮች መኖራቸውን የሚናገሩት ዳይሬክተሩ በተለይም በገበያው ወቅት ከዋጋና ከደረጃ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ጥቆማ እንደሚደርሳቸው አንስተው ባለፉት ሁለት ቅዳሜና እሁዶች ብቻ ከ48 በላይ ቅሬታዎች መቅረባቸውና በ16ቱ ላይ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡
በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ላይ የቢሮው አመራሮችን ክትትሎች እያደረገ መሆኑን የቢሮው የገበያ መረጃ ጥናት እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ሙሰማ ጀማል ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ