ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ጆሽ አቼምፖንግ በሪያል ማድሪድ እንዲሁም በሌሎች ሊጎች በጥብቅ ሲፈለግ የቆየ ተጫዋች እንደነበር አይዘነጋም። ይህ ተጫዋች ውሉ በ2026 ነው የሚጠናቀቀው ታዲያ አሁን በምዕራብ ለንደን ለተጨማሪ 5 አመት ማለትም እስከ 2029 በዚ ክለብ የሚያቆየውን ውል ፈርሟል ተብሏል።
አዲሱ ሪስ ጄምስ እየተባለ የሚጠራው አቼምፖንግ ተስፋ ሰጪ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን ከጥሩ እና አስደናቂ ክህሎት ጋር አጣምሮ የሚገኝ ተጫዋች ነው።
The አትሌቱ ጋዜጠኛ ዴቪድ ኦርነስቲን እንደዘገበው ከሆነ ተጫዋቹ ውሉን እንዲያራዝም አሰልጣኙ ኤንዞ ማሬስካ ትልቅ ሚና እንደተጫወተ ዘግቧል። ከወጣቶች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን እና አቅማቸው እንዲጎለብት የመጫወት እድልን የሚሰጥ አሰልጣኝ መሆኑን የተረዳው አቼምፖንግ ውሉን ለማደስ ይህ ጉዳይ ቁልፍ ነበር።
ከዚሁ ጎን ለጎን ዩክሬናዊው ሚካይሎ ሙድሪክ ላይ የተሰነዘረው የአበረታች ንግረ ነገር ጉዳይ እንደማያምኑ እና ሙድሪክ አሁንም ከዚ ነገር ነፃ ነው ሲሉ ከተጫዋቹ ጎን መሆናቸውን አሳይተዋል። ሁለተኛ የሽንት ናሙና የሰጠው ሙድሪክ አሁንም ምርመራው Positive ከሆነ ለ4 አመት ከእግርኳስ ሊታገድ እንደሚችል ይገመታል። የ23 አመቱ ዩክሬናዊዐፖል ፖግባ ተመሳሳይ ክስ እና ተመሳሳይ ቅጣት ሲተላለፍበት የተጪዋቹን ቅጣት ወደ 18 ወር ዝቅ እንዲል ያደረገው ተቋም ማለትም Morgan sports law የተባለውን ተቋም ጉዳዩን እንዲይዙለት ማድረጉ ተሰምቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ