ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለግዙፉ የዓለማችን ኩባንያ ጥሬ እቃ የሆኑትን ታንታለም፣ ታንግስተንና ለቆርቆሮ መስሪያ የሚያገለግለውን “ቲን” በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ከሚገኙ አካባቢዎች ወጥተው በህጋዊ መስመሮች እንዲቀርቡ እየተደረገ ነው የሚለው ክስ የቀረበው ለፈረንሳይና ለቤልጂየም ነው፡፡ የኮንጎን መንግስት ወክለው ክስ የመሰረቱት ጠበቆች ድርጅቱ የሀገሪቱ ታጣቂ ቡድኖች በሚሰሯቸው ወንጀሎች ውስጥ ተባባሪ ነው ብለዋል፡፡
አፕል ኩባንያ በጉዳዩ ላይ በሰጠው አስተያየት ክሱን ፈጽሞ ያስተባበለ ሲሆን ግብአቶቹን ኃላፊነት በሚሰማውና በህጋዊ መንገድ ብቻ እንደሚገዛ አስታውቋል፡፡ የፈረንሳይና የቤልጂየም ባለስልጣናት ጉዳዩን መርምረው ቀጣይ ሕጋዊ አካሔድ የሚያስፈልገው መሆን አለመሆኑን ይወስናሉ ተብሏል፡፡
በማዕድን ሀብቷ በበለጸገችው ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጥቂት የማይባሉ ታጣቂ ቡድኖች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ያሉ የማዕድን ሃብቶች ዘርፈውና በሕገ-ወጥ መንገድ ሽጠው በሚያገኙት ገንዘብ የወንጀል ስራቸውን የሚያስቀጥሉ ሲሆን፣ በተለይ ሕጻናትን በግዳጅ ለውትድርና መመልመላቸውና አካባቢውን መበከላቸው ትልቅ ስጋት ሆኗል፡፡
የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነን የሚሉ ተቋማት ጎረቤት ሀገር ሩዋንዳ ማዕድናቱ በሕገ ወጥ መንገድ የሚጓጓዙባት መስመር ናት ማለታቸው ይታወሳል፡፡ የሩዋንዳ መንግስት ግን ጉዳዩን ባዶ ውንጀላ ነው ሲል ያጣጥለዋል ሲል የዘገበው ዩሮ ኒውስ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ