ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተደራጀተው እና ሳይደራጁ ከህግ አግባብ ውጪ በጫኝ እና አውራጅ ስራ የተሰማሩ ወጣቶች በህግ እንዲጠየቁ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በከተማዋ ያለ-ባለቤቱ ፍቃድ ጫኝ እና አውራጆች ነን የሚሉ ግለሰቦች ለሚሰጡት አገልግሎት የተጋነነ ክፍያ በመጠየቅ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ እንግልት ሲፈጥሩ እንደነበር በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በዘርፉ ለተሰማሩ ወጣቶች መመሪያ በማውጣት በመመሪያው እንዲተዳደሩ እየተደረገ መሆኑን የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ተናግረዋል፡፡
መመሪያ ከወጣ ወዲህ ለውጦች ቢኖሩም አሁንም ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ጫኚ እና አውራጆች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
መመሪያው የህብረተሰቡን ገቢ ያማካለ አሰራር መዘርጋቱን የተናገሩት ምክትል ሀላፊው ከዚህ ውጪ በሆነ መልኩ በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ነው ያስታወቁት፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ የስራ እና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉበት አከባቢ የቁጥጥር እና ክትትል ስራው እንደሚሰራ አመላተዋል፡፡
በተመሳሳይ የኮሪደር የልማት ተነሺዎች ወደ ሚሄዱበት አከባቢ የሰላም አስከባሪ ወጣቶች እና ፖሊስ ህጉን እያስፈጸሙ እንዳሉም አስታውቀዋል፡፡
ህብረተሰቡ በራሱ አቅም የማውረድ እና የመጫን መብት እንዳለው በመመሪያ የተቀመጠ መሆኑን የገለፁት ምክትል ቢሮ ሀላፊው፤ በአስገዳጅ ሁኔታ እንሰራለን የሚሉ አካላት ካሉ ጥቆማ እንዲያቀርቡ አሳሰበዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ