ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ለአራት ቀናት የሚቆይ የሁለተኛው ዙር የልጅነት ልምሻ /ፖሊዮ/ ክትባት ዘመቻ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ሕፃናትን ለህመም፣ ለሞትና ለዘላቂ አካል ጉዳተኛነት የሚዳርግ እና ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ አደገኛ በሽታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ጤና ቢሮው በከተማዋ ለሚገኙ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት በሙሉ ክትባት በመስጠት ወረርሽኝ እንዳይከሰት ለማድረግ በሁለት ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንዳስጀመረ ተናግረዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር የክትባት መርሃ ግብር ከ691 ሺ በላይ ህፃናትን መከተብ ተችሏል ነው ያሉት።
ይህንን ሥራ ለመስራት ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ከ4ሺ 500 በላይ የሰው ሃይል በቀጥታ በዘመቻው የሚሰማራ ሲሆን በርካታ አደረጃጀት፣ በጎ ፈቃደኞች እና ባለድርሻ አካላት በድጋፍ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
ክትባቱ በተሳካ ሁኔታ ሁሉንም ህጻናት በመድረስ እንዲጠናቀቅ ወላጆችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሚና እንዲወጡ ቢሮው ጠይቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ