ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት በሰጠው መግለጫ፤ የመገናኛ ብዙሃኑን ዘገባ ተከትሎ አደረኩት ባለው ማጣራት፣ በሀገሪቱ ሕጋዊ የስደተኝነት እውቅና ኖሯቸው ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ስደተኞች አለመኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
በዚህም በሀገሪቱ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስርና እንግልት እየተከናወነ ነው በሚል በሀገር ውስጥና በውጭ መገናኛ ብዙሃን የተሰሩ ዘገባዎችን ተቋሙ መሠረተ ቢስ ናቸው ሲል አጣጥሎታል።
ስደተኞች የሀገሪቱን ሕግና ሥርዓት ጥሰው ለእስር የተዳረጉበት ሁኔታ የሚኖር ከሆነ፣ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የሚከታተለው ይሆናል ሲል አክሏል፡፡
በተጨማሪም የስደተኞች ምዝገባ ተቋርጣል በሚል የሚያሰራጨው መረጃም ሀሰተኛ ነው ያለው አገልግሎቱ፥ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የስደተኝነት መስፈርትን ለሚያሟሉ አካላት ምንም ልዩነት ሳያደርግ የምዝገባ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፤ እየሰጠም ይገኛል ብሏል፡፡
የወሳኝ ኩነት ምዝገባና የምስክር ወረቀት አገልግሎትን ጨምሮ የስደተኝነት መታወቂያ የመስጠት ተግባር ከበፊቱ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ከ26 ሀገራት ከለላና ጥበቃ ፈልገው ለመጡ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከለላና ጥበቃ እየሰጠች ትገኛለች ያለው ድርጅቱ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና ኤርትራ የሚመጡ ስደተኞች መሆናቸውን ገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ