ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መንግስት መካከል የተደረሰውን ስምምነት እንደሚደግፍ አስታወቀ።
ስምምነቱን አስመልከቶ የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ በቱርክ አደራዳሪነት በኢትዮጵያና በሶማሊያ መንግስት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ኢጋድ በአዎንታዊ መልኩ ይመለከታዋል ብለዋል፡፡
ስምምነቱ በሁለቱ እህትማማች ሀገራት መካከል የቆየውን ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር እና የሀገራቱን የሁለትዮሽ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል፡፡
ስምምነቱ እንዲፈፀም የሁለቱ ሀገራት መሪዎችን እንዲወያዩ በማድረግ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉት የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ምስጋና አቅርበዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ