ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለም አቀፉ ገበያ ላይ በበላይነት ያለው የመገበያያ ገንዘብ የሀገራቱን የፖለቲካ ሁኔታ የሚወስን እንደመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ከበለጸጉ ሀገራት ጋር የምታደርገውን የንግድ እና የውጭ ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጥንቃቄ መምራት እንደሚገባት ምሁራን ገልጸዋል።
በሀገር ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶች እና መፈናቀሎች የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲያሽቆለቁል እንደሚያደርግ የተናገሩት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እና ተመራማሪ ዶ/ር አብዱ ሞሐመድ ናቸው፡፡
በተለያዩ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የአገር ውስጥ ኢኮኖሚ ሲጎዳ ብድር እና እርዳታ የምንጠይቃት አሜሪካ በቅርቡ 49ኛ መሪ አድርጋ የመረጠቻቸው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የብሪክስ አባል ሀገራት ላይ ያላቸውን አቋም ወደ ፖሊሲ ካሳደጉት ለኢትዮጵያ ስጋት ሊሆን እንደሚችል ነው ባለሙያው የተናገሩት።
ሌላኛው የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶ/ር ቆስጠንጥንዮስ በርኸተስፋ፣ ባልተረጋጋ የኢኮኖሚ ምህዳር ውስጥ በበለጸጉ ሀገራት መካከል የሚደረገው የንግድ ጦርነት እና ማዕቀብ ሰለባ ላለመሆን ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ምርቶቻችን ገበያ በማጣት የምንዛሬ መዋዥቅ እንዳያጋጥም ለሀገር እንዲሁም ለዜጎች የመኖር ህልውና አደጋም እንደይፈጠር ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በሃያላን ሀገራት የኃይል ፍትጊያ እና የንግድ ፉክክር ለአንዱ የመወገን አጣብቂኝ ውስጥ ላለመግባት እና በቀዝቃዛው ጦርነት የደረሰብን ኪሳራ አሁንም እንዳይደገም፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ የምጣኔ ሀብት ዲፕሎማሲውን በጥልቀት መፈተሽ እና ቅድመ ዝግጅት ሊደረግ እንደሚገባ ባለሙያዎች አመልክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ