ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ብቁ የሰው ሃይል እንደሌለዉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
አሁን ላይ በዘርፉ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በምሽትም የአገልግሎት ሰአቶችን ያራዘመው ቢሮው በዚያው ልክ በብቃት ተሰማርቶ አገልግሎቱን ለመቆጣጠርና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት በቂ የሰው ሃይል እንደሌለው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው ሌሊሳ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። እስካሁን ሊኖራቸው ከሚገባው የሰው ሃይል ውስጥ 60 በመቶው ብቻ እንደሆነ አቶ ደምሰው አክለው ገልጸዋል።
ባለዉ የሰዉ ሃይል ቢሮ የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዉ በዚህም በኮድ 1 የተመረጡ ፈቃድ የተሰጣቸው የተሽከርካሪ አይነቶች ብዙሃን ትራንስፖርት አማራጮች እስከ ምሽት አራት ሰአት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሚኒ ትራንስፖርት የሚባሉትን እንደ ደጋፊ አገልግሎት ሰጪ አድርገው እንደሚጠቀሙባቸው የገለጹት አቶ ደምሰው በዚሁ መንገድ የተገልጋዮችን ቅሬታ ለመቅረፍ እየተሞከረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
እስካሁን ባለው ሂደት የብዙሃን ትራንፖስርት አገልግሎት ሰጪ አውቶብሶች ከመነሻ ካልሞላ የማይወጡበት ሁኔታ ነበር በዚህም ምክንያት ተሳፋሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡበት እንደነበር አንስተዉ በሰዓት የተገኙ ተሳፋሪዎች ይዞ አግልገሎት እንዲሰጥ ማሻሻያ መደረጉን አስገንዝበዋል፡፡
ታሪፍ፣ ታፔላዎችንና የትራንስፖርት ስምሪት ሂደቶችን በሚመለከት በዲጂታል አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመድረስ እየተሰራ እንደሆነ የገለጹት አቶ ደምሰው፤ በቅርቡ በአራተኛው ሩብ አመት የባለስልጣኑ ዲጂታል ሲስተምና የመረጃ ድረ-ገጽ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
አዲሱ ሲስተም ማንኛውም ተገልጋይ ዜጋ ከትራንስፖርት ጋር በተገናኘ በስልኩ አማካኝነት በቀጥታ ካለበት ሆኖ መረጃ የሚያስተላልፍበት መሆኑን እና የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ ቅሬታዎችን ለመቀነስና ምላሽ ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ