ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ የጎረቤት ሀገራት ዜጎች በፍርድ ቤት ተገቢው ቅጣት እየተሰጣቸው አለመሆኑን የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ በርካታ የጎረቤት ሃገራት ዜጎች የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለማውጣት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ተቋሙ በተሳሳተ መልኩ የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ዜጎችን እንደያዘ ገልጸዉ ወደ ፖሊስ እና ፍርድ ቤቶች ሲሄዱ ግን ተገቢዉን የህግ ተጠያቂነት ቅጣት ባለማግኘታቸው ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል ብለዋል፡፡ ተቋሙ ይህን ለመከላከል ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ ዜጎችን አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ የሚመለከታቸው አካላትም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ እንስቃሴ መጀመሩን አመላክተዋል፡፡
የጎረቤት አገራት ዜጎች የኢትዮጵያን ፓስፖርት ማውጣት ያስቻላቸውን የአሠራር ክፍተት፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ተቋም በፍጥነት ማስተካከያ እንዲደርግ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ላይ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ባካሄደው ክዋኔ ኦዲት የተለዩ ግኝቶችን ሲገመግም ማሳሰቡ አይዘነጋም፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ