ኅዳር 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ በ2018 ዓ.ም እንደሚደረግ ቢጠበቅም በአንዳንድ ክልሎች ያለው የሰላም እጦት በትኩረት የማይሰራበት ከሆነ በሀገራዊ ምርጫው ላይ እክል ሊፈጥር እንደሚችል መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታውቀዋል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ፤ ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ፓርቲያቸው ሙሉ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ቢሆንም አሁን ድረስ እንደ ሀገር በአንዳንድ አከባቢዎች እየተስተዋለ ያለው የጸጥታ ችግር አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል ነው ስጋታቸውን ያስቀመጡት፡፡
በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው የተናገሩት አቶ ማሙሸት፤ በቅድሚያ ግን በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት የማስፈኑ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የጋምቤላ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሳይመን ቱት በበኩላቸው፤ ፓርቲያቸው ለ7ተኛው ሃገራዊ ምርጫ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንዳለ ገልጸዋል፡፡ እንደ ፓርቲ በመልካም አስተዳደር፤ ልማት እና ሰላምን በመሳሰሉ ትልልቅ አገራዊ ጉዳይ ላይ ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ቦርዱ በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ድጋፍ እንደሚደርግ ተናግረዋል፡፡
ፓርቲዎች እጩ ተወዳዳሪዎቻቸውን ማቅረብ እንዲችሉ እንዲሁም ቅስቀሳም ማድረግ በሚችሉባቸው መንገዶች ሁሉ ቦርዱ አብሯቸው እንደሚሰራ ነው ያመላከቱት፡፡
በ2018 ዓ.ም 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚከናወን የሚጠበቅ ሲሆን በፖለቲካ ምህዳሩ እና በምርጫ ስነስርዓቱ ላይ ክፍተቶች እንዳይፈጠሩ በሀገሪቱ ሰላም የማስፈን ስራ ትኩረት እንደሚሻ ተገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ