ኅዳር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሀገራዊ ጥቅም ያላቸውን ትላልቅ ጥናቶችን ለማከናወን የበጀት እጥረት ተግዳሮት እንደሆነበት የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
የምርምር ስራ ከሚጠይቀው ወጪ አንጻር የሚመደበው በጀት እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ እና ይህ አይነቱ አካሄድም ትላልቅ ሀገራዊ ምርመሮችን ለመስራት ተግዳሮት እንደፈጠረ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አለበል ደሴ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ አብዛኛውን በጀት የሚሸፍነው በራሱ መንገድ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ በጀት የማፈላለጉ ስራን ከተለያዩ አለም አቀፍ ረጂ ተቋማትና ሀገራት ጋር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
በመንግስት በኩል እስከ 100 ሚሊዮን ብር ድረስ እንደሚመደብ የገለጹት አቶ አለበል፤ይሁን እንጂ ገንዘቡ ከፍተኛ ወጪ ለሚፈልገው ሀገራዊ ትላልቅ የምርምር ስራ እጅግ አነስተኛ ነው ብለዋል።
እያንዳንዱ የተናጠል የምርምር ስራ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚፈልግ የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ በስራው ግዝፈት እና በሚጠይቀው ወጪ ልክ የተፈቀደ በጀት አለመኖሩ ተግዳሮት ፈጥሯል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ በራሱ በጀት የማፈላለግ ጥረት በአመት ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ብር እንደሚያገኝ ያስታወቁት ኃላፊው፤ በተጨማሪም በምርምር ስራዎቹ ውጤት ምክንያትም የሚገኙ የገንዘብ ሃብቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ ኢንስቲትዩቱ ካሉት በርካታ ሰራተኞችና ከተልዕኮው ስፋትና ትልቅነት አንጻር በመንግስት የሚመደበው በጀት እጅግ አነስተኛ መሆኑን እና በአሰራር መጓተት ምክንያትም የተመደበውን በጀት በአግባቡ ለመጠቀም ምቹ ሁኔታዎች እንደሌሉ አስረድተዋል።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ወደፊት ለሀገር ከፍተኛ ገቢን ማስገኘት የሚችል ተቋም ቢሆንም፤ አሁን ላይ እየተመደበለት ያለው በጀት በዕቅዱ ልክ የሚያሰራው እንዳልሆነ የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ መንግስት በቂ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ