ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጀመሪያ ዙር ለ75ሺሕ፤ በሁለተኛው ምዕራፍ 1መቶ ሺሕ፤ በሶስተኛው ዙር ደግሞ 150 ሺሕ ተዋጊዎች ተሃድሶ እንደሚሰጥ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡
በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀምር የተገለፀው ይህ የተሃድሶ ስልጠና ለስድስት ቀናት እንደሚቆይም ብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው አስታውቋል።
መግለጫውን የሰጡት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን 371 ሺህ የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎች በስድስት ክልሎች ውስጥ እንዳሉና ከእነዚህም ወስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት 274 ሺህ የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎች በትግራይ ክልል ዉስጥ እንደሚገኙ አመላክተዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ በሰባት ክልሎች የሚገኙ ከ371 ሺህ በላይ የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከ760 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሆነ ወጭ በሁለት አመታት ውስጥ ትጥቅ የማስፈታትና መልሶ የማቋቋም ስራዎችን ለማስራት የሚስችል ቅደመ ዝግጅት ማጠናቀቁንም አስረድተዋል፡፡
መርሃ ግበሩን በሶስት ምዕራፍ ለማጠናቀቅ መታቀዱን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፤ በመጀመሪያ ምዕራፍ ለ75 ሺህ በ2ኛው ምዕራፍ ለ1 መቶ ሺህ በ3ኛው ምዕራፍ ደግሞ ለ150 ሺህ ተዋጊዎች ተሃድሶ እንደሚሰጥ አመላክቷል።
በመጀመሪያ ምዕራፍም በትግራይ ክልል ለሚገኙና ከባድ ጉዳት ለገጠማቸዉ እንዲሁም ለሴቶች ፤ በእድሜ ለገፉና ሙሉ ጤንናት ላይ ለሚገኙ ለ75 ሺህ የቀድሞ ታዋጊዎች መሆኑን አብራረተዋል፡፡
በአንድ ጊዜ 75 ሺህ ታጣቂዎችን ማስተናገድ ስለማይቻል ተከፋፍሎ በተዘጋጀዉ መርሃ ግብር መሰረት እንደሚሰለጥኑ ተናግረዋል፡፡ የቀድሞ ታዋጊዎች ትጥቅ የማስፈታት ስራ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡
የተሃድሶ ስልጠናው በዙር በዙር እየሆነ ለ75 ሺዎቹም እንደሚሰጥና በስድስት ቀን የተሃድሶ ቀናት ቆታቸው የቀድሞ ተዋጊዎቹ የሳይኮ -ሶሻልና የሲቪክ ተሃድሶ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ እንደሚደረግም አክለዋል ተናግረዋል፡፡ በትግራይ ክልል የተሃድሶ ስልጠናው በሶስት ቦታዎች የሚሰጥ ሲሆን መቐለ ፣ እዳጋሀሙስና አድዋ መሆናቸወን አስረድተዋል
ኮሚሽኑ አሁን ላይ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል ውስጥ የትጥቅ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኙ አካላት በሙሉ ወደ ሠላማዊ መንግድ እንዲመለሱና ኮሚሽኑም መልሶ የማቋቋም ስራዎችን ለማስራት ዝግጁ መሆኑን ዋና ኮሚሽነር ተመሰገን ጥላሁን አረጋገጠዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ